ተግባርና ሃላፊነት
1.3.4 የተቋሙ ስልጣንና ተግባር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን እንደገና ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 105/2011 አንቀጽ 6 መሰረት የሚከተሉት ስልጣን እና ተግባር አሉት 1. ይግባኝ የቀረበበትን ጉዳይ መርምሮ ውሳኔውን ያሻሽላል፤ያፀናል፤ ወይም ይሽራል፤ እንደሁም በአስፈላጊ የሆነውን ተጨማሪ ትዕዛዝ ይሰጣል፤ የሰጠውን ውሣኔና ትዕዛዝ ያስፈፅማል፤ 2. ግብ አስተቢዉ መ/ቤት የሰጠውን የታክስ ውሳኔ በመቃወም የሚቀርብለትን ይግባኝ በመስማት በፍሬ ነገር ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፤ 3. አግባብ ባለው ህግ መሰረት ያልቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት ያለማግኘቱን በአንድ ወር ውስጥ ለይግባኝ ባይ በጽሁፍ ያሳውቃል፤ 4. በህግ ይግባኝ በተፈቀደባቸው የማዘጋጃ ቤት ታክስና ቀረጥ ላይ የሚቀርብለትን ይግባኝ መርምሮ ይወስናል፣ 5. በዳኞች የተፈረሙ ውሳኔ ለተከራካሪ ወገኖች ይሰጣል፤ 6. በቀረበለት ጉዳይ ላይ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት አግባብነት ያለው ማናቸውም መፅሃፍ፣መዝገብ ሌላ ፅሁፍም ሆነ ማንኛውም ዓይነት ሌላ ማስረጃ (የኤሌክትሮኒከስ መረጃን ጨምሮ) እንዲቀርብለት ትዕዛዝ ይሰጣል፤ 7. በቀረበው ይግባኝ ተገቢ ውሳኔ ለመስጠት አስፈላጊ የሆነ ሰው ቀርቦ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ይሰጣል፤ 8. ከቀረበው ጉዳይ ጋር በማዛመድ ጭብጥ ላይ ተገቢውን ውሳኔ ለመስጠት የሚያስፈልገውን ማናቸውም ትዕዛዝ ለአንድ ወይም ለሁሉም ተከራካሪ ወገኖች ወይም ለማናቸውም ሰው ይሰጣል፤ 9. በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 129 የተደነገገው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የችሎት ክርክር በሚካሄድበት ወይም ጉዳይ በሚሰማበት ወቅት የችሎት መድፈር ድርጊት በፈፀመው ተከራካሪ ወገን ወይም በሌላ ሰው ላይ እስከ ብር 2500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ) የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ ይሰጣል፤ 10. በቂ ባልሆነ ምክንያት የችሎቱን ትዕዛዝ ያልፈጸመ ተከራካሪ ወገን ለሌላ ተከራካሪ ወገን ተመጣጣኝ ኪሳራ እንዲከፍል ይወስናል፤ 11. አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የሰጠውን ውሳኔና ትዕዛዝ የፖሊስ ሃይል በማዘዝ ያስፈጽማል፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን እንደገና ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 105/2011 አንቀጽ 6 መሰረት የሚከተሉት ስልጣን እና ተግባር አሉት
1. ይግባኝ የቀረበበትን ጉዳይ መርምሮ ውሳኔውን ያሻሽላል፤ያፀናል፤ ወይም ይሽራል፤ እንደሁም በአስፈላጊ የሆነውን ተጨማሪ ትዕዛዝ ይሰጣል፤ የሰጠውን ውሣኔና ትዕዛዝ ያስፈፅማል፤
2. ግብ አስተቢዉ መ/ቤት የሰጠውን የታክስ ውሳኔ በመቃወም የሚቀርብለትን ይግባኝ በመስማት በፍሬ ነገር ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፤
3. አግባብ ባለው ህግ መሰረት ያልቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት ያለማግኘቱን በአንድ ወር ውስጥ ለይግባኝ ባይ በጽሁፍ ያሳውቃል፤
4. በህግ ይግባኝ በተፈቀደባቸው የማዘጋጃ ቤት ታክስና ቀረጥ ላይ የሚቀርብለትን ይግባኝ መርምሮ ይወስናል፣
5. በዳኞች የተፈረሙ ውሳኔ ለተከራካሪ ወገኖች ይሰጣል፤
6. በቀረበለት ጉዳይ ላይ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት አግባብነት ያለው ማናቸውም መፅሃፍ፣መዝገብ ሌላ ፅሁፍም ሆነ ማንኛውም ዓይነት ሌላ ማስረጃ (የኤሌክትሮኒከስ መረጃን ጨምሮ) እንዲቀርብለት ትዕዛዝ ይሰጣል፤
7. በቀረበው ይግባኝ ተገቢ ውሳኔ ለመስጠት አስፈላጊ የሆነ ሰው ቀርቦ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ይሰጣል፤
8. ከቀረበው ጉዳይ ጋር በማዛመድ ጭብጥ ላይ ተገቢውን ውሳኔ ለመስጠት የሚያስፈልገውን ማናቸውም ትዕዛዝ ለአንድ ወይም ለሁሉም ተከራካሪ ወገኖች ወይም ለማናቸውም ሰው ይሰጣል፤
9. በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 129 የተደነገገው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የችሎት ክርክር በሚካሄድበት ወይም ጉዳይ በሚሰማበት ወቅት የችሎት መድፈር ድርጊት በፈፀመው ተከራካሪ ወገን ወይም በሌላ ሰው ላይ እስከ ብር 2500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ) የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ ይሰጣል፤
10. በቂ ባልሆነ ምክንያት የችሎቱን ትዕዛዝ ያልፈጸመ ተከራካሪ ወገን ለሌላ ተከራካሪ ወገን ተመጣጣኝ ኪሳራ እንዲከፍል ይወስናል፤
11. አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የሰጠውን ውሳኔና ትዕዛዝ የፖሊስ ሃይል በማዘዝ ያስፈጽማል፤